የቤተክርስቲያን ስነመለኮታዊ አቋም
1. ስለ መጽሐፍ ቅዱስ
መፅሐፍ ቅዱስ በእግዚአብሔር መንፈስ መሪነት የተፃፈ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን እናምናለን፣ እንዲሁም መፅሐፍ ቅዱስ ሊታመንበት የሚገባ በሰው ልጅ እምነትና ህይወት ላይ የመጨረሻ ስልጣን ያለው የቤተክርስቲያን እምነትና ሥርዓት መሠረት እርሱ ብቻ መሆኑን እናምናለን (1 ተሰሎንቄ 2:13፣ ዮሃንስ 1:1፣ 2 ጢሞቴዎስ 3:16-17)
2. ስለ እግዚአብሔር
ዘላለማዊ በሆነ፣ ነገሮች በማይወሰንት፣ ፍጹም በማይለወጥ ራሱን በሦስት አካል በአብ፤ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ በሚገልጽ በአንድ አምላክ ሁሉን በፈጠረ በእግዚአብሔር አብ እናምናለን (ዮሐንስ 1፡1-5, ዮሐንስ 10፡30)
3. ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እና ስለ የምጽአት ቀን
ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን፣ ከድንግል ማርያም መወለዱን፣ ፍፁም አምላክ ፍፁም ሰው መሆኑን፣ ስለ ሐጢያታችን በመስቀል የተሰቀለ፣ የተሰቃየ፣ የሞተ፣ የተቀበረ፣ በሦስተኛውም ቀን ከሞት በአካል ተነስቶ ለሰዎች ተገልጦ በክብር ወደ ሰማይ ያረገ መሆኑን አሁንም በአባቱ ቀኝ ተቀምጦ ዘውትር ስለ እኛ እንደሚማልድልን ። እንዲሁም መንግስቱን ለመመስረት ዳግመኛ በታላቅ ክብር እና ስልጣን እንደ ሚመለስ፣ ሙታንን እንደሚያስነሳና ለዘላለም በሚኖሩትና በሚሞቱት ላይ ፍርድን እንደሚሰጥ፣ ሐጢያተኞች ከእግዚአብሔር ፊት ተለይተው በገሃነመ እሳት እንደሚቃጠሉ፣ ፃድቃን ግን ከእርሱ ጋር ለዘላለም እንደሚኖሩ እናምናለን። (ማቴዎስ 24፡30፣ የሐዋርያት ሥራ 1፡11፣ ራእይ 19፡11-16 ፣ ራእይ 20፡11-15 ፣ ማቴዎስ 24፡30-31፣ ራእይ 1፡7፣ የሐዋርያት ሥራ 1፡10-11)
4. ስለ በመንፈስ ቅዱስ
በመንፈስ ቅዱስ አፅናኝ በአማኞች ውስጥ አድሮ መንፈሳዊ ስጦታዎችንና ሃይልን በማከፋፈል ቤተክርስቲያንን እንደሚቀድስና ዓለምን ስለ ኣጢያት፣ ስለ ፅድቅና ስለ ፍርድ እንደሚወቅስ እናምናለን፣ እንዲሁም መንፈስ ቅዱስ ሰዎችን በሃይል እንደሚያጠምቅና በልዩ ልዩ የጸጋ ስጦታዎች እንደሚሞላ እናምናለን። (የሐዋርያት ሥራ 2፡1-4፣ ዮሐንስ 14፡26፣ የሐዋርያት ሥራ 4፡31)
5. ስለ ሰው
ሰው በእግዚአብሔር አምሳል መፈጠሩን ፣ በኣጢያት መውደቁንና በዚህም ምክንያት የእግዚአብሔር ቁጣና ፍርድ ያለበት መሆኑን እናምናለን። (ዘፍጥረት 1፡27፣ ቆላስይስ 3፡10፣ ሮሜ 3፡23፣ ዮሃንስ 1፡8፣ ሮሜ 5፡12-19)
6. ስለ ደህንነት እና የዘላለም ህይወት
ደህንነትና የዘላለም ህይወት በክርስቶስ ኢየሱስ እንጂ በሌላ በማንም እንደማይገኝ እናምናለን ። (ዮሃንስ 14:6፣ ሓዋርያት 4:12፣ ዮሃንስ 3:16፣ ዮሃንስ 3:36)
7. ስለ ውሃ ጥምቀት
በእውቀት ላይ በተመሰረተ ና በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በሚደረግ የአማኝ የውሃ ጥምቀት እናምናለን ። ( ማቴዎስ 28፡19፣ ሮሜ 6፡4)
8. ስለ የጌታ እራት
ጌታችንና መዳኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ እኛ እንደሞተ የምናስታውስበትንና እንዲሁም ጌታ እስኪመጣ ሞቱንና ትንሳኤውን ለመናገር ከምዕመናን ጋር ያለውን ህብረት ለመግለፅ የጌታን እራት በመውሰድ እናምናለን ። (ማቴዎስ 26፡26-28፣ ሉቃ 22፡19-20)
9. ስለ ከሞት በኋላ ሕይወት
በሙታን ትንሳኤ በሃጢያት ላይ በሚያደርሰው የዘላለም ፍርድና አማኞች በሚቀበሉት የዘላለም ሕይወት እናምናለን ። (1ኛ ተሰሎንቄ 4፡16-17፣ 1ኛ ቆሮንቶስ 15፡52-53)
Statement of Faith
- The Holy Bible
We believe the Bible is the Word of God, written under the guidance of the Holy Spirit. It is trustworthy, authoritative, and the foundation of the church’s faith and practice. (1 Thessalonians 2:13; John 1:1; 2 Timothy 3:16–17) - God
We believe in God the Father, eternal and unchanging, who created all things and reveals Himself in the Trinity: Father, Son, and Holy Spirit. (John 1:1–5; John 10:30) - Jesus Christ and His Second Coming
We believe Jesus Christ is the Son of God, born of the Virgin Mary, fully God and fully man. He died on the cross for our sins, suffered, was buried, and rose bodily on the third day. He ascended into heaven, where He now intercedes for us at the right hand of the Father. We believe He will return in glory and power to establish His kingdom, raise the dead, and judge all humanity—rewarding the righteous with eternal life and condemning sinners to eternal fire. (Matthew 24:30–31; Acts 1:11; Revelation 19:11–16; Revelation 20:11–15) - The Holy Spirit
We believe the Holy Spirit indwells believers, sanctifies the church, distributes spiritual gifts, convicts the world of sin, righteousness, and judgment, and empowers God’s people with strength and grace. (Acts 2:1–4; John 14:26; Acts 4:31) - Humanity
We believe Humans are created in God’s image, fell into sin, and as a result is under God’s judgment. (Genesis 1:27; Colossians 3:10; Romans 3:23; John 1:8; Romans 5:12–19) - Salvation and Eternal Life
We believe salvation and eternal life are found only in Jesus Christ. (John 14:6; Acts 4:12; John 3:16, 36) - Baptism
We believe in water baptism by faith, done in the name of the Father, the Son, and the Holy Spirit. (Matthew 28:19; Romans 6:4) - The Lord’s Supper
We believe in sharing the Lord’s Supper to remember His death and resurrection, and to proclaim His coming again. (Matthew 26:26–28; Luke 22:19–20) - Life After Death
We believe in the resurrection of the dead, eternal judgment on sin, and eternal life for believers. (1 Thessalonians 4:16–17; 1 Corinthians 15:52–53)
